የአጽናፈ ሰማያችንን እጅግ አስገራሚ እና ኃይለኛ የብርሃን ፍንዳታዎች ለሁለት አስርት ዓመታት ሲያጠና የቆየው የናሳው ኒል ጌህረልስ ስዊፍት ኦብዘርቫቶሪ ታሪካዊ ተልዕኮውን በይፋ አጠናቋል። ይህ አንጋፋ የህዋ ቴሌስኮፕ የመሬትን ስበት መቋቋም ባለመቻሉ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሰዓት 9:39 ገደማ በኢንዶኔዥያ ሱማትራ አየር ክልል ላይ ወደ ከባቢ አየር ተመልሶ በመግባት በከፍተኛ የሙቀት መጠን ተቃጥሎ ፍጻሜውን አግኝቷል። ይህ ክስተት በጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማ ከነበሩት ተልዕኮዎች አንዱን መደምደሚያ ያመላክታል።
ስዊፍት በጠፈር ውስጥ ምን ሲሰራ ቆየ?
እ.ኤ.አ በ2004 ወደ ጠፈር ከተመጠቀበት ጊዜ ጀምሮ፣ የስዊፍት ዋነኛ ተልዕኮ ከታላቁ ፍንዳታ(Big bang) ቀጥሎ በአጽናፈ ሰማያችን ውስጥ የሚከሰቱትን ታላላቅ እና እጅግ ኃይለኛ የሆኑ የጋማ ጨረር ፍንዳታዎችን መከታተል እና ማጥናት ነበር። እነዚህ አስፈሪ ፍንዳታዎች በአብዛኛው የሚፈጠሩት ግዙፍ ኮከቦች የህይወት ዘመናቸውን ጨርሰው ሲሞቱ ወይም ኒውትሮን ኮከቦች እርስ በእርስ ሲጋጩ ነው።
ስዊፍት ኦብዘርቫቶሪን ከሌሎች የህዋ ቴሌስኮፖች ልዩ የሚያደርገው ዋነኛ ባህሪው "ፍጥነቱ" ነበር። በህዋ ውስጥ ድንገተኛ ፍንዳታ ሲከሰት፣ ይህ ቴሌስኮፕ ክስተቱን በሰከንዶች ውስጥ በመለየት የራሱን አቅጣጫ በፍጥነት በማዞር መረጃ ይሰበስባል። ፍንዳታውን በኤክስ-ሬይ፣ በልዕለ ሃምራዊ እና በኦፕቲካል ካሜራዎቹ አማካኝነት ይመለከት ነበር። በዚህ ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሙ፣ ብላክ ሆሎች አቅራቢያቸው የሚገኝን አንድን ኮከብ ወደ ውስጣቸው ሲስቡ እና ሲቦጫጭቁ የሚፈጠረውን እጅግ አስፈሪ የኃይል መለቀቅ በተደጋጋሚ መዝግቧል። እንዲሁም አንድ ግዙፍ ኮከብ ፈንድቶ ሱፐርኖቫ ሲፈጠር ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ መመልከት የቻለው ይኸው ቴሌስኮፕ ነበር።
Universe TodayCaught in the Act: Astronomers See Supernova As it Explodes
ቴሌስኮፑ ለምን ወደ መሬት ተፈጠፈጠ?
ቴሌስኮፑ ከተቀመጠበት ምህዋር ወርዶ ወደ መሬት ፍጥነቱን እንዲያዘቀዝቅ ያደረገው ዋነኛው ምክንያት እየጨመረ የመጣው የፀሐይ እንቅስቃሴ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የፀሐይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ መፈጠሩን ተከትሎ፣ የመሬት የላይኛው ከባቢ አየር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰፋ አድርጎታል። ይህ የከባቢ አየር መስፋፋት በቴሌስኮፑ ላይ ከፍተኛ የአየር መጎተት እና ግጭት ሊፈጥር ችሏል።
ስዊፍት እንደሌሎች ዘመናዊ መንኮራኩሮች በራሱ ሞተር ተጠቅሞ አቅጣጫውን እና ከፍታውን ማስተካከል የሚችልበት የውስጥ ኃይል አልነበረውም። በመሆኑም ይህ የከባቢ አየር ግፊት ቀስ በቀስ ወደ መሬት በከፍተኛ ፍጥነት እንዲጠጋ አስገደደው።
የከሸፈው የ30 ሚሊዮን ዶላር የማዳን ተልዕኮ
የስዊፍት ምህዋር ማሽቆልቆልን የተገነዘበው ናሳ፣ ይህን ታሪካዊ ቴሌስኮፕ ለማዳን ያልተለመደ እና ደፋር ውሳኔ አሳልፎ ነበር። በ2025 ናሳ ካታሊስት ስፔስ ከተባለ የግል የጠፈር ኩባንያ ጋር በመተባበር 'ሊንክ' የተሰኘ ሮቦቲክ መንኮራኩር በማዘጋጀት የማዳን ተልዕኮ አቀደ። የዚህ 30 ሚሊዮን ዶላር የፈጀው ተልዕኮ አላማ፣ ሊንክ ወደ ጠፈር ተጉዞ ስዊፍትን በሮቦት እጆቹ በመያዝ ገፍቶ ወደ ከፍተኛ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምህዋር ማውጣት ነበር።
en.wikipedia.orgSwift boost mission - Wikipedia
ይሁን እንጂ በሐምሌ ወር 2026 ሊንክ ወደ ህዋ ቢመጥቅም፣ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ከባድ የቴክኒክ ችግር ሊያጋጥመው ችሏል። አቅጣጫን የሚቆጣጠሩት የኤሌክትሮኒክስ አካላቱ በመበላሸታቸው መንኮራኩሩ የራሱን ሚዛን መጠበቅ አቅቶት በህዋ ላይ መሽከርከር ጀመረ። በዚህም የተነሳ ስዊፍትን ለማዳን የተደረገው ጥረት ከሽፎ፣ ተልዕኮው በይፋ ተሰረዘ። ሊንክ እራሱ በመስከረም ወር ወደ ከባቢ አየር ተመልሶ የተቃጠለ ሲሆን፣ ይህም የስዊፍትን የመጨረሻ እጣ ፈንታ የሞት ፍርድ አደረገው።
የመጨረሻው ጉዞ እና መቃጠል
የማዳን ተልዕኮው መክሸፉን ተከትሎ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ስዊፍት በሰከንድ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን እየተጓዘ የከባቢ አየራችንን ጥሶ ገባ። ከከባቢ አየር ሞለኪውሎች ጋር በፈጠረው እጅግ ከፍተኛ ግጭት የተነሳ በሺዎች ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚቆጠር ሙቀት ተፈጥሮ አብዛኛው የብረት እና የኤሌክትሮኒክስ አካሉ በአየር ላይ ቀልጦ ብናኝ ሆኗል። ናሳ እንዳስታወቀው ጥቂት ክብደት ያላቸው እንደ ቲታኒየም ያሉ አካላቱ ከቃጠሎ ተርፈው በውቅያኖስ ውስጥ ሊወድቁ ቢችሉም፣ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ያደረሰው አደጋ የለም።
NASA ScienceNASA’s Swift Observatory Re-Entered Atmosphere - NASA ScienceNASA’s Neil Gehrels Swift Observatory re-entered Earth’s atmosphere Wednesday, almost 22 years after launch. At launch, Swift was a first-of-its-kind