Back to Blog

ከምድር በላይ የሚንሳፈፈው ቤተ-ሙከራ፡ ISS ለምን ተሰራ? ምንስ አተረፍን?

ከምድር በላይ የሚንሳፈፈው ቤተ-ሙከራ፡ ISS ለምን ተሰራ? ምንስ አተረፍን?

ከራሳችን በላይ 400 ኪሎሜትር ርቀት ላይ፣ በሰዓት 28,000 ኪሎሜትር እየከነፈ የሚሽከረከር ግዙፍ ሰው ሰራሽ "ኮከብ" አለ። ይህ አለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ወይም International Space Station (ISS) ይባላል። መጠኑ የአንድ እግር ኳስ ሜዳን ያክላል፤ በውስጡም ከ20 ዓመታት በላይ የሰው ልጅ ሳይቋረጥ ኖሮበታል።ግን ለምን ተሰራ? በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጪ ፈስሶበት እዛ ላይ እንዲንሳፈፍ የተደረገው ለምንድን ነው? ከዛስ ምን አተረፍን? የሚሉትን ጥያቄዎች እንመልከት።ክፍል 1፡ ISS ለምን ተሰራ?የጠፈር ጣቢያው ግንባታ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1998 ሲሆን፣ ዋና ዓላማዎቹ ሶስት ናቸው።1. ክብደት አልባ (Microgravity) ቤተ-ሙከራበመሬት ላይ ልንሰራቸው የማንችላቸውን ሳይንሳዊ ሙከራዎች ለመስራት ነው። በመሬት ላይ "ስበት" (Gravity) ሁሉም ነገር ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። እሳትን ብትለኩሱ፣ የእሳቱ ነበልባል ወደ ላይ ይወጣል፤ ውሃ ብታፈሱ ወደ ታች ይወርዳል። በISS ላይ ግን "ማይክሮ ግራቪቲ" ስላለ፣ እሳት ክብ ሆኖ ነው የሚነደው፤ ውሃም እንደ ኳስ ይንሳፈፋል።ይህ ልዩ ሁኔታ ሳይንቲስቶች የነገሮችን ባህሪ (ፈሳሾችን፣ ሴሎችን፣ ፕሮቲኖችን እና እፅዋትን) ያለ ስበት ተጽእኖ አጥርተው እንዲያጠኑ አስችሏቸዋል። ለምሳሌ፡ የመድሃኒት ቅመማ እና የካንሰር ህክምና ጥናቶች በመሬት ስበት ምክንያት የሚዛቡትን የሴሎች አቀማመጥ እዛ...

Exclusive

Premium Story

Unlock this article and explore the universe with an ESSS membership.

BECOME A MEMBER
Already a member? Log in

People Also Like