ወደ ጦማር ይመለሱ

የጨረቃን "ምስጢራዊ ዋሻዎች" ለመዳሰስ የተፈበረከው "ተጣጣፊው" ጎማ

የጨረቃን "ምስጢራዊ ዋሻዎች" ለመዳሰስ የተፈበረከው "ተጣጣፊው" ጎማ

የጨረቃን ገመና የሚሸፍኑት ዋሻዎች፦ ከምንመለከተው እና ገደላማ ከሆነው የጨረቃ ወለል በስተጀርባ፣ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የላቫ ቱቦዎች (Lava tubes) እና ጥልቅ ዋሻዎች ተደብቀዋል። እነዚህ ተፈጥሮአዊ ዋሻዎች ለወደፊት የሰው ልጆች የጨረቃ ላይ ሰፈራ ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። እንዴት ቢባል? ከጠፈር ከሚመጣ አደገኛ ጨረር (Cosmic radiation) እና ከከባድ የሙቀት መለዋወጥ ለመሸሸግ እንደ ተፈጥሮአዊ መጠለያ ስለሚያገለግሉ ነው።ነገር ግን አንድ ትልቅ ችግር አለ፤ ወደ እነዚህ ዋሻዎች መግባት "ከሩቅ አይንህን ግንባር ያድርገው" እንደሚባለው አይነት ፈተና ነው። የዋሻዎቹ አፍ በድንጋዮች የተሞላ፣ ተዳፋቱ የከበደ እና ለመውረድ አደገኛ ነው።የሮቨሮች (Rovers) አጣብቂኝ፦ ለጨረቃ ፍለጋ ሳይንቲስቶች የሚመርጡት ትናንሽ ሮቨሮችን (ተሽከርካሪዎችን) ነው። ምክንያቱም ብዙ ትናንሽ ሮቨሮችን መላክ፣ አንድ ትልቅ ሮቨር ከመላክ ይልቅ ለአደጋ አይጋለጥም። "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲሉ፣ ብዙ ሆነው ከተላኩ አንዱ ቢበላሽ ሌላው ስራውን ይቀጥላል። ነገር ግን አንድ ትልቅ ሮቨር ከተላከ እና እርሱም ከተበላሸ፣ ሙሉ ተልዕኮው ከሽፈ ማለት ነው።ሆኖም ትናንሾቹ ሮቨሮች አንድ የራሳቸው ችግር አለባቸው። ጎማቸው ትንሽ ስለሆነ፣ ከጎማቸው ወገብ የሚበልጥ ድንጋይ ወይም እንቅፋት ሲያጋጥማቸው መሻገር አይችሉም።በጨረቃ ገጽ ላይ የሚገኝ የላቫ ቱቦ/ ዋሻ (ምን...

Exclusive

Premium Story

Unlock this article and explore the universe with an ESSS membership.

BECOME A MEMBER
Already a member? Log in

ሰዎች እነዚህንም ወደዋል